Tuesday, March 12, 2013
Monday, March 4, 2013
"ዐ ም ሐ ራ " የ ሚ ለ ው :ቃ ል: ት ር ጉም:
"ዐ ም " :ማ ለ ት :"ሕ ዝ ብ ": ሲ ሆ ን
"ሓ ራ ":ማ ለ ት :ደ ግ ሞ : "ነ ፃ ":ማ ለ ት:ነ ው ::
ዐ ም ሐ ራ :የ አ ን ድ :ጎ ሣ :ወ ይ ም :የ አ ን ድ :ነ ገ ድ :ወ ይ ም :የ አ ን ድ :ዘ ር :ወ ገ ን :አ ይ ደ ለ ም ::የ ቃ ሉ :ፍ ቺ :እ ን ደ ሚ ያ መ ለ ክ ተ ው :ዐ ም ሐ ራ :በ ኢ ት ዮ ጵ ያ :ም ድ ር :የ ሠ ፈ ሩ :ከ ተ ለ ያ ዩ :ጎ ሣ ዎ ች :ነ ገ ዶ ች :ዘ ሮ ች :ባ ህ ሎ ች :እና /ወ ይ ም :ሃ ይ ማ ኖ ቶ ች :የ ተ ወ ጣ ጡ :ወ ን ዶ ች ና :ሴ ቶ ች :እር ስ :በ እር ሳ ቸ ው :በ መ ጋ ባ ት :በ ሥ ጋ :አ ን ድ :የ ሆ ኑ ት :ህ ል ው ና :ነ ው ::በ መ ን ፈ ስ ም :ቀ ድ ሞ :በ ኪ ዳ ነ :ል ቦ ና :ቀ ጥ ሎ :በ ኪ ዳ ነ :ኦ ሪ ት :በ መ ጨ ረ ሻ :በ ኪ ዳ ነ :ም ህ ረ ት :የ ክ ር ስ ት ና :ተ ዋ ህ ዶ :ሃ ይ ማ ኖ ት :ከ እግ ዚ አ ብ ሔ ር :በ መ ወ ለ ድ :ሥ ጋ ቸ ው ና :ነ ፍ ሳ ቸ ው :እነ ር ሱ ም :ሁ ላ ቸ ው :በ አ ን ዱ :መ ን ፈ ስ :ቅ ዱ ስ :ፍ ጹ ም :አ ን ድ :የ ሆ ኑ በ ት :ሕ ይ ወ ት :ነ ው ::በ አ ጠ ቃ ላ ይ :"ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት ":የ ተ ባ ለ ው ን :ዘ ላ ለ ማ ዊ :የ ህ ል ው ና :ዓ ላ ማ :በ ሕ ያ ው ነ ት :ከ ግ ብ :ለ ማ ድ ረ ስ :መ ለ ኮ ታ ዊ ው ን :ጥ ሪ :በ ፈ ቃ ዳ ቸ ው :ተ ቀ ብ ለ ው :ለ እር ሱ :በ ጋ ራ :ቃ ል :ኪ ዳ ን :የ ገ ቡ ና :ለ ሰ ው ም :ሆ ነ :ለ ዲ ያ ብ ሎ ስ :ተ ገ ዢ :ከ መ ሆ ን :ነ ፃ :ወ ጥ ተ ው :በ እግ ዚ አ ብ ሔ ር :ሕ ገ :መ ን ግ ሥ ት :በ እኩ ል ነ ት :ፍ ት ሕ :በ መ መ ራ ት :እየ ተ ዳ ደ ሩ :እን ደ አ ን ድ :ቤ ተ ሰ ብ :የ ሚ ኖ ሩ በ ት:ሥ ር ዓ ተ :ሀ ገ ር :ነ ው :: "ኢ ት ዮ ጵ ያ :የ ዓ ለ ሙ :መ ፋ ረ ጃ" :ከ ተ ሰ ኘ ው :የ ን ቡ ረ :እድ :ኤ ር ም ያ ስ :ከ በ ደ :ወ ል ደኢ የ ሱ ስ :መ ፅ ሃ ፍ :የ ተ ወ ሰ ደ :ነ ው ::
"ዐ ም " :ማ ለ ት :"ሕ ዝ ብ ": ሲ ሆ ን
"ሓ ራ ":ማ ለ ት :ደ ግ ሞ : "ነ ፃ ":ማ ለ ት:ነ ው ::
ዐ ም ሐ ራ :የ አ ን ድ :ጎ ሣ :ወ ይ ም :የ አ ን ድ :ነ ገ ድ :ወ ይ ም :የ አ ን ድ :ዘ ር :ወ ገ ን :አ ይ ደ ለ ም ::የ ቃ ሉ :ፍ ቺ :እ ን ደ ሚ ያ መ ለ ክ ተ ው :ዐ ም ሐ ራ :በ ኢ ት ዮ ጵ ያ :ም ድ ር :የ ሠ ፈ ሩ :ከ ተ ለ ያ ዩ :ጎ ሣ ዎ ች :ነ ገ ዶ ች :ዘ ሮ ች :ባ ህ ሎ ች :እና /ወ ይ ም :ሃ ይ ማ ኖ ቶ ች :የ ተ ወ ጣ ጡ :ወ ን ዶ ች ና :ሴ ቶ ች :እር ስ :በ እር ሳ ቸ ው :በ መ ጋ ባ ት :በ ሥ ጋ :አ ን ድ :የ ሆ ኑ ት :ህ ል ው ና :ነ ው ::በ መ ን ፈ ስ ም :ቀ ድ ሞ :በ ኪ ዳ ነ :ል ቦ ና :ቀ ጥ ሎ :በ ኪ ዳ ነ :ኦ ሪ ት :በ መ ጨ ረ ሻ :በ ኪ ዳ ነ :ም ህ ረ ት :የ ክ ር ስ ት ና :ተ ዋ ህ ዶ :ሃ ይ ማ ኖ ት :ከ እግ ዚ አ ብ ሔ ር :በ መ ወ ለ ድ :ሥ ጋ ቸ ው ና :ነ ፍ ሳ ቸ ው :እነ ር ሱ ም :ሁ ላ ቸ ው :በ አ ን ዱ :መ ን ፈ ስ :ቅ ዱ ስ :ፍ ጹ ም :አ ን ድ :የ ሆ ኑ በ ት :ሕ ይ ወ ት :ነ ው ::በ አ ጠ ቃ ላ ይ :"ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት ":የ ተ ባ ለ ው ን :ዘ ላ ለ ማ ዊ :የ ህ ል ው ና :ዓ ላ ማ :በ ሕ ያ ው ነ ት :ከ ግ ብ :ለ ማ ድ ረ ስ :መ ለ ኮ ታ ዊ ው ን :ጥ ሪ :በ ፈ ቃ ዳ ቸ ው :ተ ቀ ብ ለ ው :ለ እር ሱ :በ ጋ ራ :ቃ ል :ኪ ዳ ን :የ ገ ቡ ና :ለ ሰ ው ም :ሆ ነ :ለ ዲ ያ ብ ሎ ስ :ተ ገ ዢ :ከ መ ሆ ን :ነ ፃ :ወ ጥ ተ ው :በ እግ ዚ አ ብ ሔ ር :ሕ ገ :መ ን ግ ሥ ት :በ እኩ ል ነ ት :ፍ ት ሕ :በ መ መ ራ ት :እየ ተ ዳ ደ ሩ :እን ደ አ ን ድ :ቤ ተ ሰ ብ :የ ሚ ኖ ሩ በ ት:ሥ ር ዓ ተ :ሀ ገ ር :ነ ው :: "ኢ ት ዮ ጵ ያ :የ ዓ ለ ሙ :መ ፋ ረ ጃ" :ከ ተ ሰ ኘ ው :የ ን ቡ ረ :እድ :ኤ ር ም ያ ስ :ከ በ ደ :ወ ል ደኢ የ ሱ ስ :መ ፅ ሃ ፍ :የ ተ ወ ሰ ደ :ነ ው ::
Friday, February 1, 2013
╬╬╬ ጥር 24 የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ስባረ አጽማቸው ነው፤ በረከታቸው ይደርብን፡፡ ╬╬╬
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል፡፡ መዝ 34፣19
ጥር 24 የኢትዮያዊው ጻድቅ ብጹእ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ስባረ አፅማቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት አክብራ የምትውልበት ታላቅ ቀን ነው።አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን
አጥተዋል። ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22
ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ከዚያም ለ7
ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ
ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል።
ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር
ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24
ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና
አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው
ያስቧት አሜን!!
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል፡፡ መዝ 34፣19
ጥር 24 የኢትዮያዊው ጻድቅ ብጹእ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ስባረ አፅማቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት አክብራ የምትውልበት ታላቅ ቀን ነው።አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል።
ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን!!
“ዘይሁብ መርሐ ርቱዓ ለቤተክርስቲያን”
በጸሎተ ኪዳን ዘሠርክ ላይ እንደተነገረው፥
ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ለምትሆን፥ ጸጋን ኃይልን ለምታድል፥ አምነው ለሚቀርቡት ምስጋና አንድም በሃይማኖት ለሚገኝ ክብር ማረፊያ
ማሳረፊያ ላደረጋት ለቤተክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። የተገረፈላት፥ሥጋውን የቆረሰላት፥ ደሙን ያፈሰሰላት፦ ነፍሱንም
አሣልፎ የሰጠላት እርሱ ነውና። የሐዋ ፳፥፳፰።
ጥንት ሙሴን እና አሮንን ልጆቹንም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የመረጠ
እግዚአብሔር ነው። ዘጸ ፫፥፩-፳፪፣ ፳፰፥፩-፲፬ ። ይህንን ምርጫ ለመቃወም ወይም በምርጫው ጣልቃ ለመግባት የሞከሩ ዳታን፥ ቆሬንና
አቤሮን ፍጻሜያቸው አላማረም። “እናንተ የሌዊ ልጆች ስሙኝ፤ የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን የእግዚአብሔርን
ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ እንድታገለግሏቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱ ታላችሁን?” ብሎ
የመከራቸውን ሙሴን አልሰሙትምና ዘኁ ፲፮፥፩-፶። ከቤተ መንግስቱም ሰዎች እነ ዖዝያን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ገፍተው ቤተ መቅደሱን
ደፍረው ነበር። “ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፥ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ
ወደ መቅደስ ገባ ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። ንጉሡንም ዖዝያንን
እየተቃወሙ፥ ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተቀደሱት ለአሮን ልጆች ለካህናቱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ አይገባህም፥ ከእግዚአብሔር
ርቀሃልና ከመቅደሱ ውጣ፥ ይህ በአም ላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ክብር አይሆንህም፥አሉት፤” ይላል። የንጉሡም መጨረሻ አላማረም።
፪ኛ ዜና ፳፮፥፲፮-፳፫
እግዚአብሔር እርሱ ራሱ የመረጣችውንም ቢሆን የሚቀጣበት ጊዜ አለ።
“የቅርብ ጠበል ልጥ ያርሱበታል፤ ዝቋላ የቅርቡ ያርሰዋል፥ የሩቁ ይሳለመዋል።’’ እንዲል፥ ቤተ እግዚአብሔርን
ደፍሮ ማስደፈር በቀረቡት የሚብስበት ጊዜ አለና ነው። የሊቀ ካህናቱ የአሮን
ልጆች ናዳብና አብድዩ እግዚአብሔር ባላዘዛቸው እሳት፥ የእምነቱ ሥርዓት በማይፈቅደው መን ገድ የዕጣን መሥዋዕት
በማቅረባቸው በሞት
ተቀጥተዋል። ‘’እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ በላቸው፤ (አቃጠላቸው)፤ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ” ይላል። ዘሌ
፲፥፩-፪ ።
ሙሴና አሮንም በሕዝቡ ገልበጥባጣነት እጅግ የተቆጡበት ጊዜ ስለነ በረ፥ “ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ
በእኔ አላመናችሁምና፥ስለዚህ
ወደሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛች ሁ አትገቡም።” ተብለዋል። የእግዚአብሔር ቃል ነውና ከነዓን አልገቡም። ዘሌ
፲፥፩-፲፫
የሊቀ ካህናቱ የዔሊ ልጆችም በቅድ ስናው ሥፍራ ርኵሰትን ይፈጽሙ ነበር። አባታቸው ‘’ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ
እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፥ ሰው እግዚአ ብሔርን
ቢበድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸልዩለታል?’’ ቢላቸውም አልሰሙትም። ‘’እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው
ወድዶአልና የአባታቸውን
ቃል አልሰሙም። ‘’ ይላል። እግዚአብሔርም፥ ‘’ያከበሩኝን አከብራለሁ፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።
እነሆ፥ ዘርህንም
የአባትንም ቤት ዘር የማጠፋበት ዘመን ይመጣል፤ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። በዓይኖቹ የሚፈጽም በነፍሱም
የሚተጋ ሰውን
ከመሠዊያዬ አላጠፋም። ከቤትህ የሚቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጎልማሶች ሰይፍ ይሞታሉ።‘’ ብሎ ተናገረ። ፩ኛ ሳሙኤል
፪፥፳፪-፴፮ የተናገረውም
ጊዜውን ጠብቆ በልጆቹ ላይ ተፈጸመ። ዔሊም “በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለምን በክፉ ዓይን ተመለከትህ?
የእስራኤል ልጆች በፊቴ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳማያቱ ስለ አከበርኩህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን
ለምን መረጥህ?” ተብሎ ነበርና የልጆቹን መርዶ እንዲሁም የታቦተ ጽዮንን በአሕዛብ እጅ መማረክ ሰምቶ፥ ከወንበሩ
ወድቆ፥ አንገቱ
ተቆልምሞ አጉል ሞት ሞቷል። እናታቸውም ይህንኑ ሰምታ በወሊ ድ ላይ ሞታለች። ፪ኛ ሳሙ ፪፥ ፳፱፣ ፬፥፩ በአዲስ
ኪዳንም አገልጋዮችን
ይመርጥ የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‘’አሥራ ሁሉቱን ደቀመዛሙርቱን ጠርቶ ያወጡአቸው ዘንድ፥ በርኵሳን
መናፍስት ላይ ሥልጣንን ሰጣቸው።‘’ ይላል። የሐዋ ፲፥፩። ከዓለም ለይቶ የመረጣቸውን
እነዚህን ‘’እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ ፍሬም እንድ ታፈሩ፥ ፍሬአችሁም
እንዲኖር ሾምኋችሁ።
እርስ በእርሳችሁም እንድትዋደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ‘’ ብሎአችኋል። ዮሐ ፲፭፥፲፮። ቅዱሳን ሐዋርያት የተከተሉት
ይኽንኑ መንገድ ነው። “እንግዲህ ከዮሐንስ
ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት
ዘመን ሁሉ ከእኛ
ጋር አብረው ከነበሩት ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል፤’’ አሉ። ኢዮስጦስ
የሚሉትን በርናባስ
የተባለውን ዮሴፍን እና ማትያስን ሁለቱን ሰዎች አቆሙ፥ እንዲህም ብለው ጸለዩ፥ “አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ፥
ከእነዚህ ከሁለቱ
የመረ ጥኸውን አንዱን ግለጥ። ይሁዳ ወደ ገዛ ሀገሩ ይሄድ ዘንድ
የተዋትን ይህቺን የአገልግሎትና የሐዋርያነትን ቦታ የሚቀበላትን ግለጥ፤” አሉ። ዕጣም አጣጣሏቸው፥ ዕጣውም በማትያስ
ላይ ወጣ፥
ከአሥራ አንዱ ሐዋርያትም ጋር ተቆጠረ፥” ይላል። ማትያስን በዕጣ የመረጠ እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም ቅዱሳን
ሐዋርያት ዕጣ ያጣጣሏቸው
እግዚአብሔር እንዲመርጥ ነውና። የሐዋ ፩፥፳፪-፳፮። “በአንጾኪያ በነበረችው ቤተክርስቲያን ነቢያትና መምህራን
ነበሩ፤ እነርሱም
በርናባስ፥ ኔጌር የተባ ለው ስምዖን፥ የቄሬናው ሉቅዮስ፥ ከአራተኛው ክፍል ገዢ ከሄሮድስ ጋር ያደረው ምናሔ፥
ሳውልም ነበሩ። የእግዚአብሔርን
ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ፥ በርናባስን እና ሳውልን እኔ ለፈለግኋችሁ ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ያን ጊዜም ከጾ
ሙና ከጸለዩ፥
እጃቸውን በራሳቸው ላይ ከጫኑባቸው በኋላ ላኩአቸው።” የሚልም አለ። የሐዋ ፲፫፥፩-፲፫። ሲሞን መሠሪ ይህችን
የእግዚአብሔር ምርጫ
የሆነች ሥልጣን እንደ ሸቀጥ ለመሸመት ሞክሮ አልተሳካለትም። ቅዱስ ጴጥሮስ፥ “የእግዚ አብሔርን ጸጋ በገንዘብ
ልትገዛ አስበሃልና
ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። በዚህ ነገር ዕድልና ርስት የለህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ልብህ የቀና አይደለምና።
አሁንም ከክፋትህ
ተመለስና ንስሐ ግባ፥ የልቡናህንም ሃሳብ ይተውልህ እንደሆነ እግዚአ
ብሔርን ለምን፤ በመራራ መርዝ ተመርዘህ፥ በዓመፃ ማሰሪያ ተተብትበህ
አይሃለሁና።” ብሎታል። የሐዋ ፰ ፥ ፲፭ – ፳፬። በመጨረሻም በምትሐት ዐርጋለሁ ብሎ በሞከረ ጊዜ፥ ቅዱስ ጴጥሮስ
ቢያማትብበት
ወድቆ ተንቀጫቅጮ ሞቷል።
እንግዲህ አባቶችም ልጆችም የምናውቀውና የምናምነው እውነት ይኽንን
ቢሆንም፥ በቤተክርስቲያናችን የሚታ የውና የሚሰማው ሁሉ ግን ከዚህ እውነት እየራቀ ለመምጣቱ ምስክር መጥቀስ አያሻም። መንግስታት
በተለዋወጡ ቁጥር በተፅዕኖ ቀኖና ቤተክርስቲያን እየፈረሰ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ፀሐይ የሞቀውን እውነት መሸፈን አይቻልም።
የቤተክርስቲያንን መሪዎች የሚመርጠው እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ሌላ ኃይል ከሆነ ሊቀ ካህናቱ ዔሊ እንዳደረገው እግዚ አብሔርን ማሳነስ
ነው። እንደ ንጉሡ ዖዝያን እግዚአብሔርን መድፈር ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ተቀምጦ ከእንደዚህ አይነቱ ግብር ጋር መተባበርም እንደ
ዳታንና አቤሮን፥ እንደ ቆሬን ፥ እንደ አፍኒንና ፍንሐስ፥ እንደ ናዳብና አብድዩም መሆን ነው። በዚህን ጊዜ ለቤተክርስቲያን እንደ
ሙሴ እና እንደ አሮን ያለ ሰው ያስፈልጋታል። በዖዝያን ዘመን እንደ ነበሩት ያሉ ጽኑአን የሆኑ ካህናት ያስፈልጓታል። እንደ ቅዱስ
ጴጥሮስ ያለ ሐዋርያ ጠበቃ ሆኖ ሊቆምላት ይገባል።
ለጥፋቱ ለብቻው የሚጠየቅ ክፍል የለም፥ ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን። ቅዱስ ዳዊት “ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፥ አንድስ እንኳን በጎ ነገርን
የሚያደርጋት የለም።” ብሎአልና። መዝ ፶፪፥፫። የቤተክርስቲያኒቱ ችግር የሰነበተ እንጂ አዲስ አይደለም። ያለፉትን ሃያ ዓመታት
ልዩ የሚያደርገው ግን ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ፥ የአገር ቤት ሲኖዶስ፥ የው ጭው ሲኖዶስ፥ የሀገር ቤቱ ፓትርያርክ፥ ስደተኛው ፓትርያርክ መባሉ ነው። በዚህ ክስተት የተጎዳችው ቤተክርስቲያኒቱ
ብቻ ሳትሆን ሀገሪቷም ጭምር ናት። ክስተቱንም ይዞ የመጣው የመንግሥት ለውጥ መሆኑ ሁሉም የሚያምንበት ነው። አንድ መታወቅ የሚገባው
ትልቅ ጉዳይ ቢኖር፥ የዚህች ቤተክርስቲያን ጉዳይ የአርባ አምስት ሚሊዮን ምእመናን (ሕዝብ) ጉዳይ እንጂ የጥቂቶች ብቻ አለመሆኑን
ነው። የአንድ ሰው ድምፅ እንኳ ሊከበር ይገባል በሚባልበት ዓለም
ተቀምጠን የዚህን ሁሉ ሕዝብ ድምፅ አልሰማም ማለት ምንም አይጠቅምም። በመሆኑም የቤተክርስትያኒቱ ልዩነት ወደ ከፋ ደረጃ ከሚያደርስ
ተግባር ተቆጥበን ለዕርቅና ለሰላሙ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል።
እርቅን የምንፈጽመው ፥ ሰላምንም የምናመጣው ቀድሞም ለምን ተነካን?
አሁንስ ለምን እንነካለን? በሚል መንፈስ ሳይሆን በዚህ ምክንያት የሚመጣ ጉዳት ካለም ስለ ቤተክርስቲያን ብለን በመታገሥ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ የታረቀን ሰላም ንም የሰጠን መከራ መስቀልን ታግሦ በመስቀል ላይ በፈጸመው ቤዛነት ነውና። እኛ በበደልን እርሱ
ክሶ ነውና። ሁላችንም ልንከተለው የሚገባን መንገድ ይህ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “በድላችሁ የመጣባችሁን ብትታገሡ፥ ምስጋናችሁ
ምን ድን ነው? ነገር ግን መልካም እየሠራችሁ የደረሰባችሁን ግፍ ብትታገሡ ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የምታስመሰግን ይህች ናት። ለዚህ
ተጠርታችኋልና፤ ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአል። እርሱም ኃጢአት አልሠራም፥
በአንደበቱም ሐሰት አልተገኘበትም። ሲሰድቡት አልተሳደበም ፥ መከራ ሲያጸኑበት አልተ ቀየመም፥ ነገር ግን እውነተኛ ፍርድን ለሚፈርደው
አሳልፎ ሰጠ። ከኃጢአታችን ያወጣን ዘንድ በጽድቁም ያድነን ዘንድ እርሱ ስለ ኃጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ። በግርፋቱም
ቁስል ቁስላችሁን ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘ በዙ ነበርና፥ አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛ እና ጠባቂ ተመለሱ።” ብሎአል። ፩ኛ
ጴጥ ፪፥፳-፳፭።
ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ
ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ
ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት
ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን
በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ
ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው።
አንድነቱ ይምጣ እንጂ መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። በመሆኑም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ይህን ወስነናል፤”
እንድትሉን እስከ መጨረሻው ተስፋ እናደርጋለን። በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን
ይሰጣታል። ቤተክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች። አባቶቻችንም በጥቅምትና በግንቦት ሲኖዶስ ይታይ የነበረው
የእርስ በርስ ሙግት ይቀርላችኋል ። እኛም አባቶቻችን ተሰባስበው ተጨቃጨቁ ከሚለው ሰቀቀን እንድናለን። ሃይማኖት አጽንተው ሥርዓት
ወስነው አስተዳደሩን አስተካክለው በፍቅር ተለያዩ ብለን በአራቱም መዓዝን እንሰ ብካለን። እናንተም በሚቀጥለው ስብሰባ እስክትገናኙ
ትነፋፈቃላችሁ። እንዲህ ሲሆን በመካከላችሁ ነፋስ አይገባም። ማንም ተነሥቶ ቀን ከፈለኝ ብሎ “ጳጳሳቱ አይረቡም” አይላችሁም። ዓለም
ይፈራችኋል እንጂ አትፈሩትም። “እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት” ትሉታላችሁ። እንደ አባቶቻችሁ አራዊቱ እንኳን ይታዘዙላችኋል። ልዑላን
ትሆናላችሁ። ስለሆነም፥ ለራሳ ችሁም፥ ለቤተክርስቲያናችሁም፥ ታሪክ ሠርታችሁ እለፉ፥ እኛንም የአባቶቻችንን ገድል ለመጻፍ የበቃን
እንሆን ዘንድ አድርጉን። ይህ ካልሆነ ግን አድሮብን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ያዝንብናል። ኤፌ ፬፥፴።
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን።| ጸሎተ ሐሙስ |
|
|
በሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ
ጸሎተ ሐሙስ ነቢያት በሀብተ ትንቢት በመንፈሰ ትንቢት
‹‹እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት›› /መዝ. 117፥24/ በማለት ትንቢት የተናገሩላት በቤተ ክርስቲያናችን
አስተምህሮ ትላልቅ የተባሉ ምሥጢራት የተፈጸሙባት ዕለት ናት፡፡
“እግዚአብሔርም በግብጽ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ይህ ወር የወሮች የመጀመሪያ ይሁናችሁ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፡፡ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ፡፡ የቤቱ ሰዎች ቁጥርም ለጠቦቱ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደነፍሶቻቸው ቁጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ፡፡ የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰዱ በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛ ቀን ድረስ ጠብቁት፡፡ የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት፡፡ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቀቡት፡፡ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ ከመራራው ቅጠል ጋር ይበሉታል ጥሬውን በውኃ የበሰለውን አትብሉ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት ከእርሱም እስከ ጧት አንዳች አታስቀሩ እስከ ጧትም የቀረውን በእሳት አቃጥሉት ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፡፡ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው፡፡ እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ አገር አልፋለሁ… ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ /ዘዳ.12፥1-15/፡፡
“እግዚአብሔርም በግብጽ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ይህ ወር የወሮች የመጀመሪያ ይሁናችሁ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፡፡ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ፡፡ የቤቱ ሰዎች ቁጥርም ለጠቦቱ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደነፍሶቻቸው ቁጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ፡፡ የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰዱ በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛ ቀን ድረስ ጠብቁት፡፡ የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት፡፡ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቀቡት፡፡ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ ከመራራው ቅጠል ጋር ይበሉታል ጥሬውን በውኃ የበሰለውን አትብሉ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት ከእርሱም እስከ ጧት አንዳች አታስቀሩ እስከ ጧትም የቀረውን በእሳት አቃጥሉት ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፡፡ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው፡፡ እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ አገር አልፋለሁ… ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ /ዘዳ.12፥1-15/፡፡
እስራኤል ይኸንን ሥርዓት በሚፈጽሙበት ዓመታዊ በዓል ዋዜማ
ላይ ነበር ሐዋርያቱ ወደ ጌታችን ቀርበው እንዲህ ያሉት “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ልናሰናዳልህ ትወዳለህ?
እርሱም ወደከተማ ወደ አልዓዛር ቤት ላካቸው /ማቴ.20፥6-18/፡፡
አስቀድመን የገለጥነው ቃል እስራኤል ዘሥጋ ከሞተ በኩር የዳኑበት የፋሲካ በግ ምሳሌነት የሚያሳይ ነው፡፡
በጉ ነውር የሌለበት የመሆኑ ምክንያት ኀጢአት የሌለበት
የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡ በጉን በወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን እንዲሠውት እንደታዘዙ የጌታ ምክረ ሞቱ በዐሥር ተጀምሮ
በዐሥራ አራተኛው ቀን ተፈጽሟል፡፡ የበጉ ደም የተቀባበት ቤት ሞተ በኩር አልደረሰም በመስቀሉ ላይ የፈሰሰውን ቅዱስ
ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉ ክርስቲያኖችንም ሞት አይደርስባቸውም፡፡ የበጉን ሥጋ ጥሬውንና ቅቅሉን እንዳይበሉ
ጥብሱን እንዲበሉ ታዘዋል ይህም በእሳት የተመሰለ መለኮት የተዋሐደውን ነፍስ የተለየውን ሥጋና ደም ለምንቀበል
ለእኛ ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ ነው፡፡
አታሳድሩ ከአንዱ ወደሌላው አትውሰዱት መባሉ ጌታችን ሥጋው በመስቀል ላይ ላለማደሩ እና ወደ መቃብር መውረዱን የሚያስረዳ ሲሆን የበላችሁትን አታሳድሩ መባሉ ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ተረፈ መሥዋዕት አያድርምና ነው፡፡
በጸሎተ ሐሙስ የሚከተሉት ዋና ዋና ምሥጢራት ተፈጽመዋል፡-
የማይሻረው፣ ዘላለማዊው፣ ፍጹሙ፣ ኪዳን የተመሠረተበት ዕለት ነው፡፡
እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ኪዳናት የተሻሩ አሉ የማይሻሩም አሉ፡፡ የማይሻሩ ኪዳናት ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ሙሴ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ዳዊት፣ ኪዳነ ምሕረት ናቸው፡፡ የተሻሩት የደም ኪዳናት ናቸው፡፡ በደም የተመሠረቱ የብሉይ ዘመን ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳን አምላካዊ ደም ተሽሯል፡፡ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች የኀጢአት ይቅርታ የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡ /ማቴ.26፥26/ ይህ ሥርዓት የክህነቱንም ሥርዓት የቀየረ ሥርዓት ነው፡፡
እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ኪዳናት የተሻሩ አሉ የማይሻሩም አሉ፡፡ የማይሻሩ ኪዳናት ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ሙሴ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ዳዊት፣ ኪዳነ ምሕረት ናቸው፡፡ የተሻሩት የደም ኪዳናት ናቸው፡፡ በደም የተመሠረቱ የብሉይ ዘመን ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳን አምላካዊ ደም ተሽሯል፡፡ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች የኀጢአት ይቅርታ የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡ /ማቴ.26፥26/ ይህ ሥርዓት የክህነቱንም ሥርዓት የቀየረ ሥርዓት ነው፡፡
ቅዱስና ያለተንኮል ነውርም የሌለበት ከኀጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል፡፡ እርሱም አስቀድሞ ስለራሱ ኀጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ አይገባውም፡፡ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህንን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና” /ዕብ.7፥27/ ተብሎ የተነገረለት የሐዲስ ኪዳን የክህነት ሥርዐት ነው፡፡ ስለዚህ አስቀድሞ የነበረው የእንስሳት ደም ተሽሮ አማናዊ የሆነው የክርስቶስ ደም የተተካበት ዘላለማዊ ፍጹም ኪዳን የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡
አዲስ ሕይወት አዲስ ዘመን የተመሠረተበት ነው፡፡
ዘመኑ ሥያሜውን ያገኘው በዚች ዕለት ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳን
ሥርዓት መሥዋዕት የተሠራበት ዕለት ነው፡፡ ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና
እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ
ይህ ነው” ማቴ. 26፥26 ስለዚህ ሐዲስ ኪዳን የሚለው ስያሜ በዚች ቀን እንደተፈጸመ ልብ ይሏል፡፡ የቀደመው ኪዳን
እርሱም በደም የሆነው መሥዋዕትነት አለፈ በተሻለው የመረጨት ደም እርሱም በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ደም ምክንያት ዘመን ተለወጠ፣ ስያሜውንም አገኘ እርሱም ሐዲስ ኪዳን /ዓመተ ምሕረት/ ነው፡፡ የፍዳ፣ የመርገም፣
የኩነኔ ዘመን አልፎ የምሕረት፣ የነፃነት፣ የድኅነት ዘመን ተተካ፡፡
አገልጋዮቹን የለየበት ዕለት ነው፡፡
የእርሱ ገንዘብ የሆኑ ሐዋርያት እስከ ዕለተ ሞት ድረስ ይታመኑ ዘንድ አገልግሎታቸውን ያጸናበት የማይገባቸውን ወገኖች የለየበት ዕለት ናት፡፡ ይሁዳ የሐዲስ ኪዳን ሰው አልበረም “በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ፤ ሲበሉም እውነት እላችኋለሁ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል አለ፡፡ እጅግም አዝነው እያንዳንዱ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን ይሉት ጀመር፤ እርሱም መልሶ እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው አለ፡፡ /ማቴ.26፥20/ ይሁዳ በዚች ዕለት ከሐዋርየት ተለየ፤ ጌታውን ለሠላሳ ብር አሳልፎ ሰጠ፡፡ ስለዚህ የሐዲስ ኪዳን አገልጋዮች ከፍቅረ ነዋይ፣ ከአድመኝነት፣ ከምቀኝነት የራቁ፣ የተለዩ ለፈጣሪያቸውና ለአገልግሎታቸው የታመኑ እንዲሆኑ ሥርዐት ተሠራ፡፡
ሐዋርያት የተጠመቁበት ዕለት ነው፡፡
እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” ዮሐ.13፥1-10
ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም” ቁ.9/ በእርግጥም ያልተጠመቀ ከጌታ እድል ክፍል የለውም፡፡ እናም ቅዱሳን ሐዋርያት በእዚህች ዕለት የተጠመቁባት ዕለት ናት፡፡
ማጠቃለያ
ቅዱስ እግዚአብሔር አማናዊ ሥጋውን አማናዊ ደሙን የሰጠባት፣ ለሕይወት ለበረከት እንድንሆን ምሥጢሩን የገለጠባት፣ ምዕመናንን ቅዱስ ሥጋውን በልተው ክቡር ደሙን ጠጥተው በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚቀበሉባት፣ የትንሣኤውን ብርሃን በተስፋ የምንጠባበቅባት ዕለት በመሆኗ ይህች ዕለት ለእኛ ለክርስቲያኖች ልዩ የሆነ ትርጉም አላት፡፡ ዕለቷንም የምናከብረው በዚህ መንፈስ ነው፡፡
ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እስከ ዘለዓለሙ አሜን፡፡
ጥር 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
- ምንጭ፡- የበረሃው ኮከብ ቅዱስ እንጦንዮስ መጽሐፍ
Monday, January 28, 2013
| “ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ፡፡” |
|
|
በዲ/ን ሰሎሞን መኩሪያ
ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.6
በረከቱ ይደርብንና ይህንን ቃል የተናገረ የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም ወዳጅ የሆነው ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በብሉይ ዘመን በቅዱስ ዳዊት ሕይወት
የተከወነውን በምስጢር ስቦ አምጥቶ የሰማዕታትን ክብር አጎልቶ ተናግሮበታል፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊትን
እግዚአብሔር አምላክ ለእስራኤል አነገሠው፡፡ በዙሪያው የነበሩ ኤሌፍላዊያንን አጥፍቶ ደብረ ጽዮንን /መናገሻ
ከተማውን/ አቅንቶ ሲኖር ከዕለታት አንድ ቀን ዳዊት ታመመ፡፡የዳዊትን መታመም ሰምተው፣ ካሉበት ተነስተው የዳዊትን
ከተማ በተለይም ቤተልሔምን ከበቧት፡፡ ዳዊት ይህ ሰምቶ “ወይ እኔ ዳዊት! ድሮ ታመምሁና ጠላቶቼ ሰለጠኑ ሲል
የኀያላኑን ልቦና ለመፈተን ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባመጣልኝ?” አለ፡፡ በዚህ ጊዜ የጭፍሮቹ አለቆች ሦስቱ
ማለትም አዲኖን፣ ኢያቡስቴ ኤልያና ርስታቸውን /የውኃ መያዣ/ ይዘው፣ ጦራቸውን አሰልፈው፣ ጠላቶቹን ድል ነስተው፣
ዳዊት ሊጠጣ የወደደውን ውኃ አመጡለት፡፡ቅዱስ ዳዊትም ያንን ውኃ አፈሰሰው “ለምን አፈሰስከው?” ቢሉት “ደማችሁን
መጣጠት አይደለምን?” ብሎ፤ ይህም ከጽድቅ ገብቶ ተቆጠረለት፡፡ 2ሳሙ.23፥13-17
አባቶቻችን ይህንን ሲያመሰጥሩት የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ አባታችን
አዳም ከተድላ ገነት ወደ ምድረ ፋይድ፥ ከነጻነት ወደ መገዛት፥ ከልጅነት ወደ ባርነት፥ በወረደና ፍትወታት እኩያት
ኀጣውእ በጠላትነት በተነሱበት ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተገኘ ከጌታ ጎን የተገኘ ማየ ገቦ
አመጡለት ማለትም የአዳም ልጅነት በከበረው የክርስቶስ የደሙ ፈሳሽነት የሥጋው መሥዋዕትነት ተመለሰለት፡፡ ይህንን
ለአዳምና ለልጆቹ የባህርይ አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ፀዋትወ መከራ
እያሰቡ ሰማዕታት በእግዚአብሔር ፍቅር ተቃጥለው “እግዚአብሔርን ካዱ ለጣዖት ሰገዱ” ሲባሉ “እግዚአብሔርን አንክድም
ለጣዖት አንሰግድም” ብለው ደማቸውን አፈሰሱ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረላቸው፡፡ /ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሐሙስ/
“ሰማዕት” ማለት ምስክር ማለት ነው፡፡ ይህ ደማቸውን ስለ
እግዚአብሔር ፍቅር ብሎ ማፍሰስ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረላቸው፥ የዳዊት ወታደሮች ስለ ዳዊት ፍቅር ብለው “ደማችን
ይፍሰስ” እንዲሉ፤ ዳዊትም ያመጡለትን ውኃ መጠጣት ደማችሁን እንደመጠጣት ነው ብሎ በፍቅር ምክንያት ውኃውን
እንዳፈሰሰው፥ ይህም ጽድቅ ሆኖ እንደተቆጠረለት፥ የእግዚአብሔር ወዳጆች የሆኑ ቅዱሳን ሰማዕታትም እግዚአብሔርንና
የእግዚአብሔር ሃይማኖት የሆነችው እውነተኛይቱን ሃይማኖት ወደው ደማቸውን አፈሰሱ፣ አጥንታቸውን ከሰከሱ፣ ስለዚህ
እንደ ፀሐይ አብርተው በሰማያት ዛሬም ስለ እኛ እየማለዱ አሉ፡፡ “ለመሆኑ ከዚህ ክብር የደረሱት እንዴት ነው?”
ብሎ ለሚጠይቅ ቅዱስ ኤፍሬም ሲመልስ ሦስት ነገሮችን ያነሣል፡፡
1. “ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም ናቁ” ይላል
ዓለም እንደየዘመኑ የተለያየ ጠባይ አላት፤ ልክ እንደ እስስት
ትለዋወጣለች፡፡ ስለዚህ ሁል ጊዜ ከእውነት ይልቅ ሐሰት፥ ከፍቅር ይልቅ በእውነተኞቹ ላይ ጥላቻ፥ በግልጽ
ይታይባታል፡፡ የራሷ የሆነውን እጅግ አድርጋ ትወዳለች ስለዚህም በተለያየ መረብ እያጠመደች ለዘለዓለሙ ትጥላለች፡፡
“ሰማዕታት” /ምስክሮች/ ግን የዚችን ዓለም ጣዕም ናቁ፤ ማለትም እውነት እግዚአብሔርን፥በሐሰት ጣዖት አልለወጡም
ስለዚህ በእግዚአብሔር ዘንድ በክብር ተቀምጠው ስለ እኛ እያማለዱ አሉ፡፡ ትምህርታችንን የበለጠ ግልጽ
እንዲያደርግልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ባሕር አሸዋ ቁጥራቸው ከበዛ በእግዚአብሔር ዘንድ ክብር ካላቸው ቅዱሳን
ሰማዕታት መካከል የሰማዕታት አለቃ ተብሎ በፈጣሪው በእግዚብሔር ዘንድ ስለተሾመው ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጋድሎ
ሕይወት ጥቂት እንመለከታለን፡፡
በረከቱ ይደርብንና ቅዱስ ጊዮርጊስ የአባቱ ስም ዘሮንቶስ የእናቱ
ስም ቴዎብስታ ይባላል፡፡ አባቱ በፍልስጥኤም አገር መስፍን ነበር፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕፃን ሳለ አባቱ በሞት
ተለየው ከዚያ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ሹመት ለመቀበል ወደ ዱድያኖስ ንጉሥ ዘንድ ሄደ፡፡ ንጉሡም ጣዖት አቁሞ
ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው፡፡ ይህንን አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ፤ በእርሱ
ዘንድ ያለውን ለንጉሡ እጅ መንሻ ያመጣውን ገንዘቡን ለድሆች እና ለምስኪኖች ሰጠ፡፡ ባሮችንም ነጻ አወጣቸው ከዚህ
በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ “በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ በግልጽ እኔ ክርስቲያን ነኝ” አለ፡፡
ያን ጊዜ ንጉሡ ዱድያኖስ በዘመኑ ከነበሩ በሥልጣኑ በሥሩ ከሚተዳደሩ 70 ነገሥታት ጋር ሆኖ አባብለው እግዚአብሔርን
እንዲክድ ለጣዖት እንዲሰግድ ይህንን ቢያደርግ ብዙ ብር እና ወርቅ እንደሚሰጠው ከእርሱም በታች ባለ ሥልጣን
እንደሚያደርገው ቃል ገባለት፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ይህንን አልተቀበለም፡፡ በፊቱ ናቀው እንጂ
ጌታ በቅዱስ ወንጌል እንደተናገረ “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል” ማቴ.16፥26
እንዳለ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣትነቱ እግዚአብሔርን ክዶ ለጣዖት ሰግዶ የሚያገኘውን ወርቅ እና ብር እንዲሁም
ሥልጣን ናቀ፡፡ ይህ እግዚአብሔር ለማገልገል በሕይወቱ ያሳየውን ቆራጥነት እራስን መካድን ያሳየናል፡፡
ማቴ.16፥24፡፡ ከዚህ ቅዱስ ሕይወት ተምረን እኛም በዓለም ውስጥ ከሚሠራው የኀጢአት ሥራ በንስሐ ሕይወት በጽድቅ
ሥራ መለየት ይገባናል በዘመናችንም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዓለምን ጣዕም መናቅ ማለት እውነትን በሐሰት አለመለወጥ
ማለትም እውነተኛ ሆኖ መገኘት የሚበላውን ከማይበላው ጋር ቀጥቅጦ አለመሸጥ በሚዛን አለመበደል ፍርድ አለማጉደል ጉቦ
ተቀብሎ ድኃ አለመበደል በምንሠራበት መሥሪያ ቤተ ሰነድ አለመሰረዝ አለመደለዝ ባጠቃላይ በሕይወታችን
በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ በእውነት ታምነን መገኘት ይገባናል፡፡ ለዚህም የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎትና ምልጃ
ይርዳን፡፡
2. ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው ዱድያኖስ ንጉሥ የዚችን ዓለም
ጣዕም አቅምሶ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማባበል ለጣዖት ማሰገድ በተሳነው ጊዜ የወሰደው እርምጃ በዘመኑ በነበረው የተለያየ
መሣሪያ ተጠቅሞ የቅዱስ ጊዮርጊስን ደም ማፍሰስ ነበር፡፡ በገድለ ጊዮርጊስ እንደተጻፈ ለቆመው የወርቅ ምስል
አልሰግድም እነርሱንም አላመልክም ይልቁንም ዐይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ እጅ እያላቸው የማይዳስሱ
እግር እያላቸው የማይሄዱ በአፋቸው ትንፋሽ የሌለ ግዑዛን ናቸው፡፡ እነርሱን የሚያመልኩ እንደነርሱ ይሁኑ ብሎ
በቅዱስ ዳዊት ቃል ንጉሡን እና ጣዖታቱን በዘለፈ ጊዜ መዝ.113፥12-16 ዱድያኖስ ንጉሥ ቅዱስ ጊዮርጊስን
አስገረፈው በተገረፈ ጊዜ ደሙ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከዚያም ጨለማው ጥልቅ ወደ ሆነ የእስር ቤት ጣሉት፡፡ ዱድያኖስና
ሰባው ነገሥታት በዚህ መከራ ይሞታል የእርሱን መከራ መቀበል የደሙንም መፍሰስ የተመለከቱ ሌሎች ሰዎችም በመፍራት
በእኛ የጣዖት አምልኮ ሥርዓት ፀንተው ይኖራሉ ብለው አስበው ነበር፡፡
ነገር ግን የቅዱስ ጊዮርጊስን መከራ መቀበል የደሙንም መፍሰስ
የወደደ ይህንንም ለክብር ሊያደርግለት ፈቃዱ የሆነ ቅዱስ እግዚአብሔር በግርፋቱና በደሙ መፍሰስ እንዲሞት አልተወውም
ስለዚህ ወደ እስር ቤቱ የጨለማውን ጥልቀት በብርሃን የሚገልጥ ቁስሉንም የሚፈውስ የሚያጽናና መልአክ ላከለት፤
መልአኩም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገብቶ ቁስሎቹን ፈወሰ፤ እርሱንም አጽናንቶ ፣ እግዚአብሔር ለእርሱ ያደረገለት ያለውን
ሁሉ በግልፅ ነግሮት በክብር አረገ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ሲነጋ የዱዲያኖስ ወታደሮች ወደ
ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጡ ጊዜ ምንም የግርፋትና የደም መፍሰስ ምልክት ባላገኙ ጊዜ፣ ይልቁንም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደስ
ብሎት እግዚአብሔርን ሲያመሰግን አግኝተው ተደነቁ፡፡ ከዚያም “እኛም በቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ እናምናለን፡፡”
ብለው ብዙ ሰዎች ሰማዕትነት ተቀበሉ፡፡አንድ ዛፍ በተቆረጠ ጊዜ ከስሩ ብዙ ችግኝ እንዲገኝ በቅዱስ ጊዮርጊስ መከራ
መቀበል ብዙ ሰዎች ወደ ሃይማኖት መጡ፡፡
3. ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ
ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲህ ያለውን ተአምት በማድረግ ብዙ ሰዎች ወደ
እግዚአብሔር እንደተመለሱ የተመለከተ ዱድያኖስ አሁንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ የሚደርሰውን የመከራ ስልት በመቀያየር
አትናስዮስ የተባለ ጠንቋይ አስመጥቶ መርዝ በጥብጦ እንዲጠጣ አዘዘ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም የቀረበለትን መርዝ በሰው
ሁሉ ፊት በትእምርተ መስቀል አማትቦ ባጣጣመ ጊዜ እንኳን ሊገድለው ገፁ ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርቶ ተገኘ፡፡ በዚህም
ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ላይ “በስሜ የሚያምኑትን ይህች ምልክት
ትከተላቸዋለች…የሚገድል መርዝ ቢጠጡ አይጎዳቸውም ” በማለት የተናገረው ቃል ተፈጸመለት፤(ማር.16፥18)፡፡ ይህንን
ተመልክተው ጠንቋዩን ጨምሮ ብዙ ሰዎች “በቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ እናምናለን” ብለው ከአምልኮ ጣዖት እግዚአብሔርን
ወደማምለክ ተመልሰው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
በዚህ ነገር የተበሳጨ ዱድያኖስ በብረት ምጣድ እሳት አንድደው
እንዲያቃጥሉትና ካሳረሩት በኋላ በመንኮራኩር እንዲፈጩት ከዚያም ይድረስ ወደ ሚባል ታላቅ ተራራ ወስደው በንፋስ
እንዲበትኑት አዘዘ እንደ ትእዛዙም አደረጉበት አጥንቶቹን ፈጭተው በበተኑት ጊዜ ከተራራው ሥር የነበሩ ዕፀዋት
በቅጠላቸው ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔ እያሉ ተናገሩ /መሰከሩለት/ በዚህ ጊዜ መራራ የሆነውን የሞት ጽዋ ተጎንጭቶ
ከባድ መከራ ተቀብሎ እንዲሞት የእግዚብሔር ፈቃዱ ቢሆንም የቅዱስ ጊዮርጊስን ክብር እርሱን ፍፁም መውደዱን
ለመግለጽ አምላካችን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ቅዱስት ድንግል ማርምን ባለሟሎቹ ቅዱሳን
መላእክትን ወዳጆቹ ነቢያት ሐዋርያት ቅዱሳንን አስከትሎ አፅሙ ወደ ተዘራበት ወደ ይድራስ ተራራ ወረደ በክብር
ወረደ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘው የተበተነው የወዳጄን የቅዱስ ጊዮርጊስን አፅም ስብሰባህ አምጣ አለው እርሱም
እንደታዘዘው ሰበስቦ ወደ ጌታችን አቀረበ ያን ጊዜ ጌታችን በምሕረት እጁ ተቀብሎ አዳምን የፈጠሩ እጆቼ አንተንም
የፈጠሩ አሁንም ወዳጄ ጊዮርጊስ እኔ አዝዤአለሁ ከሞት ተነሣ አለው፡፡ ያን ጊዜ ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሸራ
አምሮበት ከሞት ተነሣ ጌታችንም በአፍ መሳም ሳመው የሚጸናበትን ቅዱስ መንፈሱን አሳደረበት ከዚያም ሊቀበለው ያለውን
መከራ የሚያገኘውን ዋጋ ነግሮት በክብር አረገ፡፡
ይህ የሆነው ጥር 18 ቀን ነው፡፡ ይህንን መራራ ሞት በእሳት
መቃጠል በመንኮራኩር መፈጨት እንደ እህል መዘራት ታግሶ ከእግዚአብሔር ዘንድ በተደረገለት ተአምራት ከሞትም በመነሣቱ
ብዚ ሰዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ አምነው ወደ እውነተኛይቱ ሃይማኖት ተመልሰዋል፡፡ እንግዲህ በገድሉ መጽሐፍ
እንተጻፈ ለ7 ዓመት መራራ መራራ የሆነ ብዙ መከራዎችን ታግሶ በስተመጨረሻ በሰይፍ ተከልሎ /አንገቱን ተቆርጦ
ከአንገቱም ደም ውኃ ወተት ፈሶ ለተጋድሎው 7 የድል አክሊል ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበለ የከበረ ቃል ኪዳን
የተቀበለ ሰማዕት ነው፡፡ እኛም ከዚህ ቅዱስ ገድል ተምረን አሰረ ፍኖቱን በመከተል ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ
ሃይማኖታችንን እንድናጸና ዘመኑ የሚጠይቀውን ሰማዕትነት ምግባር ማቅናት እንድናቀና የሠማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ጸሎትና ቃል ኪዳን ተራዳኢነት አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን
አማላጅነት የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን አሜን፡፡
Subscribe to:
Comments (Atom)

